የሀዘን መግለጫ

እጩ ዶ/ር ሙሉብርሃን ሃጎስ አረፈ
ቦንጋ፤ ህዳር 30/2014 ዓ.ም (ቦ/ት/ኮ) እጩ ዶ/ር ሙሉብርሃን ሐጎስ በቦንጋ መ/ራን ትምህርት ኮሌጅ በመ/ርነት ለበርካታ ዓመታት በመ/ርነትና በተለያዩ የስራ ኃላፊነቶች ሲያገለግል የነበረና በስራውም ታታሪ፣ የመልካም ስብዕና ባለቤት፣ ሰው አክባሪና ትሁት የነበረ ሲሆን ላለፉት አራት ዓመታት ለሶስተኛ ዲግሪ ትምህርት አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከሄደ በኋላም ጭምር ስለ ኮሌጁ እድገትና ለውጥ የሚያስብና በቅርበት የሚከታተል መ/ር ነበር፡፡ በተጨማሪም መ/ሩ በህይወት ዘመኑ ከስራ ባልደረቦቹ፣ ከተማሪዎቹ ጋር፣ ከአካባቢው ማህበረሰብ፣ ከህጻናትና ከልዩ ልዩ የህብረሰተብ ክፍሎች ጋር የነበረው ጤናማ፣ የቀረበ መስተሳሰርና መስተጋብር ለሌሎች አስተማሪና ዘውትር ከህሊና የማይጠፋ ነው፡፡
ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በገጠመው የጤና እክል ምክንያት በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ህይወቱ በማለፉ የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽን ፈጣሪ ነፍሱን በአጸደ ገነት እንዲያኖራትና ለቤተሰቦቹ፣ ወዳጅ ዘመዶቹና ለስራ ባልደረቦቹ ሁሉ መጽናናት እንዲሰጥልን እንመኛለን፡፡
ህዳር 30 ቀን 2014 ዓ.ም.
የቦንጋ መ/ራን ትምህርት ኮሌጅ