የቦንጋ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ዕጩ መምህራንን በዛሬው ዕለት አስመረቀ፡፡

የቦንጋ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ዕጩ መምህራንን በዛሬው ዕለት አስመረቀ፡፡
ቦንጋ፣ ሰኔ ፣ 25፣ 2014(ቦመትኮ) የቦንጋ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ 856 ዕጩ መምህራንን በዛሬው ዕለት አስመረቀ
የቦንጋ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ባለፉት ሶስት ተከታታይ ዓመታት በመደበኛ መርሐ ግብር ያሰለጠናቸውን 856 ዕጩ መምህራንን በዛሬው ዕለት አስመርቋል።
ኮሌጁ በዛሬው ዕለት በ 20 በተለያዩ የትምህርት መስኮች 473 ወንዶችና 383 ሴት በድምሩ 856 ዕጩ መምህራንን አስመርቋል፡፡
የኮሌጁ ዲን አቶ አንተነህ አየለ ለተማሪዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸውን ባስስተላለፉበት ወቅት እንደተናገሩት ኮሌጁ በሰርተፊከት ደረጃ ለማሰልጠን ከተመሰረተበት ጊዜያት አንስቶ በመደበኛና በተከታታይ የስልጠና መረሃ ግብሮች በሰርቲፊኬትና በዲፕሎማ ደረጃ ከ38 ሺ 6መቶ 31በላይ መምህራንን በማሰልጠን ወደ መምህርነት ሙያ ማሰማራቱን ገልፀዋል።
ዲኑ አክለዉም በትምህርትና በመልካም ስነ-ምግባር የታነፀ እራሱንና ማንነቱን በዉል የተገነዘበ ትዉልድ ካልተገነባ ወደፊት እንዲኖረን የምንፈልገዉ ሀገር ሊኖረን አይችልም ሲሉ ተናግረዋል።
በመሆኑም ትዉልድና ሀገር የመገንባት ኢትዮጵያዊነትን የማስረፅ ተግባር የአንድ ወገን ተግባር ሳይሆን የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ርብርብ የሚጠይቅ እንደሆነም ገልጸዋል።
ተመራቂዎች ወደ መምህርነት ሙያው በሚሰማሩበት ወቅትም ሃገርና ህዝብ የጣለባቸውን ትውልድን የማነፅና የመቅረፅ ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጡም አሳስበዋል።
በመቀጠልም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አልማው ዘውዴ በበኩላቸዉ ሀገራችን የጀመረችዉን የብልፅግና ጉዞ ለማሳካት የተማረ ዜጋ ማፍራት አስፈላጊ ነዉ ብለዋል።
ሰለሆነም የዛሬ ተመራቂ ተማሪዎች በተማሩበት የሙያ መሰክ ሀገራቸዉን እና ህዝባቸዉን በታማኝነትና በቅንነት እንድያገለግሉ ሲሉም አሳስበዋል።
የዕለቱ የክብር እንግዳ እና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ፀጋዬ ማሞ በንግግራቸዉ በደቡብ ክልል ትምህርታችዉን ጀምራችሁ በቀድሞ የደቡብ ክልል ትምህርታችሁን ጀምራችሁ በአሁኑ በአዲሱ ክልል በመመረቃችሁ እለቱን ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።
በቀድሞ የትምህርት ስርዓተ የመጨረሻ ተመራቂ ተማሪዎች በመሆናችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ያሉት አቶ ፀጋዬ ተመራቂ ተማሪዎች ስራ ጠባቂ ሳትሆኑ ስራ ፈጣሪ ትዉልድ መሆን እንዳለባቸውም አሳስበዋል።
በመጨረሻም የኮሌጁ ምክትል ዲንና የመ/ራን ልማት ዳይሬክቶሬረት ዳይሬክተር ዶ/ር አህመድ እስማኤል የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ካስተላለፉ በኋላ በዛሬዉ እለት በ 12+3 ዲፕሎማ መርሀ ግብር በ 20 በተለያዩ የስልጠና መስኮች ያሰለጠናቸዉን ወንድ 473 ሴት 383 በድምሩ 856 ተማሪዎችን ማስመረቅ መቻሉንም ተናግረዋል።
ኮሌጁ በቀጣይ የትምህርት ዘመን በድግሪ መርሀ ግብር ትምህርት መስጠት ምልመላ በማጠናቀቅ ላይ መሆኑንም ጭምር ገልፀዋል ገልጸዋል።
ከየት/ክፍሉ አብላጫ ዉጤት ያሥመዘገቡ ተማሪዎች ሽልማት የተበረከተ ሲሆን ካጠቃላይ ከተመራቅ ተማሪዎች መካከልም ከህሳብ ክፍል ተማሪ አክሊሉ ጎበዜ 3.82 እና ከፒሪ ስኩል ክፍል ተማሪ እመቤት ሀ/ኢየሱስ 3.66 ዉጤት በማስመዝገብ የወርቅ መዳሊያ ተሸላሚዎች ሆነዋል።